በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስተዳደር ፍ/ቤት
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፐ/ሰ/የሰ/ ሀብት ልማት ቢሮ በውስጡ ያሉ ዘርፎችን ይዞ ተቋማት ለተገልጋዩ ህብረተሰብ የተሸለና ተደራሽነት ያለው አገልግሎት እንዲያገኝና መልካም አስተዳደር እንድሰፍን በሁሉም ዘርፍ እየሰራ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ከእነዚህ ዘርፎች አንዱ የአስተዳደር ፍ/ቤት ዘርፍ ስሆን በዚህ በፐ/ሰ/የሰ/ሀብት ልማት ቢሮ እንደ አንድ ዘርፍ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ የይግባኝ ሥህተቶችን ስያርምና ስሰራ የቆየበት ሁኔታ ቢኖርም ከአገልግሎት አሰጣጥ አንጻር ችግሮች እንደምስተዋሉ ቀደም ስል በነበርንበት ክልል እሮሮዎች ስሰሙ ቆቶዋል፡፡
ይሁን እንጅ አሁን ባለንበት ሁኔታ ከቀድሞ ደ/ብ/ብ/ሕ/ክልል በአድሱ አደረጃጀት ተለይተው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሆነው ወደ ስራ ከተገባበት ጊዜ ጀምሮ ይህ ፍ/ቤት ከተቋቋመበት ዓላማና ተገባር አንጻር የመንግሥት ሠራትኞችን ቅሬታ ይግባኝ የሚመረምርና በጉዳዮቹ አዋጁን፣ መመሪያንና ህግን የጣሱ ውሳኔዎችን በአግባቡ የማረምና የመናስተካከል ሥራ ከመሆኑ አንጻር ህጎች፣ አዋጆች፣ መመሪያዎችን ያልተከተለና በምጥስ ሁኔታ የሚወሰኑ የተቋማት የዲስፕሊን ውሳኔዎች አከባቢ የሚታዩ የህግ ሥህተቶችን እያረመ ይገኛል፡፡ ማረም ብቻም ሳይሆን በይግባኝ ውሳኔው ላይ ቅር የተሰኘ የትኛውም ወገን ወደሚቀጥለው መደበኛ ፍ/ቤት(ክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ) ይግባኝ የማለት መብቱ እንደሆነም ጭምር በግልጽ እየሰራ ይገኛል፡፡ በዚህ በተቋማት የዲስፕሊን ቅጣት አወሳሰን ጋር ተያይዘው የሚፈጠሩት የህግ ሥዕተቶችን ከማረም ሂደት ውስጥም በይግባኝ ባይ እና በመልስ ሰጭ ተቋማት የትኛውም ወገን መጉላላትና እንግልት ሳይዳረግ የቀረቡትን የይግባኝ አበቱታዎች በተቀላጠፈና በተፋጠና ሁኔታ በመመርመር ውሳኔ ከመስጠትም አኳያ ቀደሞ ከነበረው አሁን የተሻለ ሥራ እየተሰራ ይገኛል። የተፋጠና ሥራና የተጠፋጠና ውሳኔ መስጠት ብቻም ሳይሆን በሁለቱም ተከራካር ወገኖች መካከል በክርክር ሂደት ውስጥ የሚፈጠሩ አወዛጋቢ ጉዳዮችን ተክክለኛ ፍትህ ለመስጠት ዳኞች በችሎት አዳራሽ ውስጥ ክርክር ብቻ ታጥሮ ሳይወስኑ የጉዳዩ መነሻ በሆነው ታችኛው ተቋም ድረስ ወርደው መሬት ላይ ያለውን ነባራዊ እውነታ በመመርመርም ጭምር የተፋጠና ውሳኔ እየተሰጠ ይገኛል፤ ከዚህ በተጨማሪ በሥር ዞንና ልዩ ወረዳዎች ከዲስፕሊን ቅጣት አወሳሰንና አተገባበር በተመለከተ ያለውን ችግር ለማጥበብ ለምመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ግንዛቤ ለማስጨበጥ ባሳለፍነው 2016 ዓ/ም በጀት ዓመት ሥልጠና ሰጥተናል። አሁንም በየጊዜው ተመሳሳይ ሥልጠናዎችን ለክልል ተቋማት ጭምር ተደራሽ በማድረግ ግንዛቤ በመፍጠር ችግሮችን እየቀረፍን የምንሄድ ይሆናል፡፡
ሁሉም ተቋማት ማወቅና መያዝ የሚገባቸው ዋና ጉዳይ በድስፕሊን ቅጣት አወሳሰን እና አተገባበር ዙሪያ በሂደቱ ተቋማት የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 06/2016ን እና የዲሲፕሊን አፈጻጸም መመሪያን ባልተከተለ መልኩ የሚወስኑት ውሳኔዎች በይግባኝ ወደ አስተዳደር ፍ/ቤት ቀርቦ ስሻሩ፣ ስሻሻሉ ለተቋማት ወይም ለመንግስትም አላአስፈላግ ወጪ፤ ለባለሙያውም ላልተገባ እንግልት የሚዳረግበት ሁኔታ በሰፊው ይስተዋላል፤ በሌላ በኩል በይግባኝ ሂደቱም ላይ ከተቋሙ የሚወከሉ አንድንድ ሰዎች በህጉና በጉዳዩ በቂ እውቀትና ግንዛቤ ሳይኖራቸው ለክርክር ችሎት ስቀርቡ ይታያል፡፡ ስለዚህ ለክርክር የሚወከሉ ሰዎች በጉዳዩ ላይ በቂ እውቀት ኖሮ ተገቢውን ክርክር የሚያደርጉ መሆን ይጠበቃል፣ የተቋማት ኃላፊዎችም በተለይ በዲሲፕሊን ኮሚቴ የሚቀርቡ የውሳኔ ሐሳቦችን ከማጽደቅ በፊት ከሂደቱ ጀምሮ በአግባቡ ህጉን የተከተለ የውሳኔ ሐሳብ መሆኑን ማረጋገጥ አለባችው፡፡