Skip to main content

የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን ባወጣው አዋጅ ቁጥር 199/2015 አንቀጽ 27 ለፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሃብት ልማት ቢሮ ከተሰጡ ስልጣንና ተግባራት መካከል በአዋጁ አንቀፅ 14 ቢሮዉ   በክልሉ በየደረጀው በሚገኙ የመንግስት ተቋማት የሚታዩ የመልካም አስተዳደርና የኪራይ ሰብሳብነት ችግሮችን በጥናት መለየት፣ ለተለዩ ችግሮች መፍቻ ስልቶች መንደፍ፣ የችግሮቹን የአፈታት ሂደት መከታተልና መደገፍ፣ የፋይዳ ጥናት በማድረግ የህዝብ እርካታን ማረጋገጥ እንዲሁም በዚሁ አዋጅ አንቀፅ 9 ቢሮዉ በክልሉ መንግስት መስሪያ ቤቶች የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ፣ የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ሥርዓት መዘርጋቱንና ተግባራዊ መደረጉን እንደሚያረጋግጥ ተደንግጓል፡፡

በመሆኑም ቢሮዉ ከላይ በማቋቋሚያ አዋጁ የተሰጠዉን ስልጣንና ተግባር ለመወጣት ካደራጃቸዉ ዓላማ ፈፃሚ ዳይሬክቶሬቶች መካከል የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ድጋፍና ክትትል ዳይሬክቶሬት አንዱ ነዉ፡፡

የዳይሬክቶሬቱ ሥራ በክልሉ በየደረጃው የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደርና የክራይ ሰብሳቢነት ችግሮችን ለመለየት የሚያስችል ጥናት በማድረግ ጀምሮ ችግሮቹን ለመቅረፍ የሚያስችሉ አሰራሮችና አደረጃጀቶችን በመቅረጽ፣ በመዘርጋትና በማስተግበር፣ ችግር ፈቺ የሆኑ የቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት፣ የአፈጻጸም ድጋፍና ክትትል በማድረግና ግብረመልስ በመስጠት እንዲሁም የተገኙ ውጤቶችን ለማወቅ የሚያስችሉ የፋይዳ ጥናቶችን በማድረግ ይጠናቀቃል፡፡

በመልካም አስተዳደር መርሆዎች ትግበራ ፣በሕዝብ ክንፍ አደረጃጀትና አሰራር፣በፀረ-ክራይ ሰብሳቢነት ትግል፣ እንዲሁም በተገልጋዮች ቅሬታ አቀራረብና አፈታት ላይ ለክልሉ የመንግስት ተቋማት የአቅም ግንባታ ስልጠና የመስጠትና አተገባበራቸዉን አስመልክቶ የፋይዳ ጥናት እና ለተቋማት ድጋፋዊ ክትትል አገልግሎቶች በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ድጋፍና ክትትል ዳይሬክቶሬት ከሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸዉ፡፡ 

በሴክተሩ በ2022 ተልዕኮውን በውጤታማነት መፈጸም የቻለ፣በሥነ-ምግባሩ የተመሰገነ ፤ነጻ፣ገለልተኛና ብቃት ያለው የመንግሥት አገልግሎት ዘርፍና አገልጋይ ዕውን ሆኖ ለማየት ራዕይ አስቀምጦ እየተሰራ ነዉ፡፡

በመሆኑም በክልሉ በየደረጃዉ የሚገኙ የመንግስት ተቋማት የተቋቋሙለትን ዓላማ ለማሳካት በሚሰሯቸዉ ስትራቴጂክ ስራዎችም ይሁን በየዕለቱ በሚሰጠዋቸዉ አገልግሎቶች 8ቱን የመልካም አስተዳደር መርሆዎችን አክብረዉ፣የየተቋማቸዉን የህዝብ ክንፍ ለይተዉ አብቅተዉና አሳትፈዉ እንዲሁም የተገልጋዮችን ቅሬታ በተዘረጋዉ የአሰራር ስረዓት መሰረት በመፍታት የተገልጋዮቻቸዉን እርካታ ለማሳደግ እንዲሰሩ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን፡፡