Skip to main content

የሰው ሀብት አሰተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት

የሥራ አመራር ዋና ሥራ  አስፈጻሚ  ሆኖ የመንግሥት ሠራተኞችን አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ በመከተል የሚከተሉትን አብይ እና ቁልፍ ተግባራት  ያከናውናል፡፡

  •      የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ተግባራት ያቅዳል፣ ያደረጃል፣ ይመራል፣ይከታተላል፣ ይደግፋል፣ ይወስናል ይቆጣጠራል፣ የስራ  አፈጻጸም  ይገመግማል፣ ክፍተቶችን ይለያል፣ ያበቃል፤

  •      የሰው ኃይል ልማት የሚመራ ገዢ ስትራቲጂና ዝርዝር ዐቅዶች እንዲዘጋጁና ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፤

  •      ከስትራቴጂክ ዕቅድ የተመነዘረ ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል  አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ይገመግማል፤

  •      የሰው ኃይል ልማትና አስተዳደር  የሚመለከቱ  ፖሊሲዎች፣  መመሪያዎች፣ የስራ ሂደቶች፣ ማዕቀፎችን እንዳግባቡ ተዋደውተቀርጸው ተግባራዊ እንዲሆኑ ይመራል ይቆጣጠራል፤

  •      በሚሰጠው የሥልጣን ውክልና መሠረት በሰው ሀብት ሥራ አመራርና አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፣ ወይም የሚሰጡ  ውሳኔዎችን  ተግባራዊነት ይከታተላል፤

  •      በመንግሥት ሠራተኞች መመሪያዎችና ደንቦች መሠረት ከፍተኛ አደረጃጀት ላለው ተቋም ልዩ  ልዩ የቅጥር፣ የደረጃ ዕድገት፣ ዝውውር፣ የድስፕሊን፣ የቅሬታ ማስተናገጃና እንዲሁም ሌሎች አግባብነት ያላቸው ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙና ተግባራዊ እንዲሆኑ ይከታተላል፤

  •      አዲስ ለሚቀጠሩ ሠራተኞች ስለ መንግሥት መመሪያዎችና ደንቦች እንዲሁም ተቋሙ ስለተቋቋመበትና ስለሚጠበቅበት ውጤት  እንዲሁም ስለ መሥሪያ ቤቱ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች ኃላፊነት የማስተዋወቂያ ስልጠና (`Inducation) እንዲሰጥ በማድረግ ወደ ሥራ እንዲሰማሩ ያደርጋል፤

  •      ዘመናዊ የአፈጻጸም ምዘና ግምገማና ማሻሻል ስርዓት እንዲኖረው የሚያስችል የአፈጻጸም ምዘናና አመራር ስርዓት እንዲዘጋጅና ተግባራዊ  እንዲሆን  ያደርጋል፤

  •      የሰው ኃይል ክህሎትና ብቃት ለማሳደግ የሚያስችል የሰው ኃይል ልማት  ስልጠናና ትምህርት ዕቅድና መርሃ ግብር እንዲዘጋጅና እንዲተገበር ያደርጋል፤

  •      የአመራር ብቃትና ዝግጅት ለማሳደግ የሚያስችል የተከታይ ማፍራትና የሞያ ዕድገት ስትራቴጂ፣ ዕቅድና ስርዓት ዝግጅትና ትግበራ  በበላይነት ይመራል ያስተባብራል ይቆጣጠራል፤

  •      የሰው ኃይል ልማት አገልግሎት አሰጣጥ ለማላቅ የሚያስችል የክዋኔ ትዕምርትና (operating model); የስራ ሂደት የቲክኖሎጂና የመረጃ ስርዓት ግንባታና ትግበራን 

  •      አደረጃጀትና ተቋማዊ ዕድገት ብሎም ባህል በሚፈለገው አቅጣጫ ለማጎልበት የሚያስችል ቀጣይነት ያለው የተቋማዊ አቅም ግንባታ  ማዕቀፍ፣ ስልትና ዕቅድ እንዲዘጋጅና ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፤

  •      አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከፍተኛ አደረጃጀት ላለው ተቋም የሰው ሀብት ሥራ አመራርን የተመለከቱ መመሪያዎች እንዲከለሱና አዳዲስ ጥናት  እንዲጠኑ ያደርጋል፣ የጥናት ውጤቶችን ይገመግማል፤

  •      ከፍተኛ አደረጃጀት ላለው ተቋም ለሥራ መደቦች የሥራ ትንተና ተከናውኖ የሥራ ዝርዝር መግለጫ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤

  •      ከፍተኛ አደረጃጀት ያለው ተቋም ሠራተኞች መንግሥት ባወጣው የምዘና ስርዓት መሠረት በየወቅቱ እንዲመዘኑ ያደርጋል፣ በምዘናው  ውጤት መሠረትም ቀጣይ ተግባራትን እንዲከናወኑ ያደርጋል፤