ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ
ቢሮው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፣
- የክልሉ መንግስት ፐብሊክ ሰርቪስ ብቃት ያለውና ውጤታማ መሆኑን ያረጋግጣል፣
- የክልል መንግስት ሰራተኞች ምልመላና መረጣ በብቃት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ያደርጋል፣
- የፐብሊክ ሰርቪሱ የሰው ኃይል በቀጣይነት በሚለማበት ጥቅም ላይ የሚውልበትን ስልት ይቀይሳል፣ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፣
- ፐብሊክ ሰርቫንቱ በብቃትና በአፈጻፀም ውጤታማነት ላይ የተመሰረተ የክፍያና የማበረታቻ ሥርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፣ ውጤታማነቱን ይገመግማል አስፈላገጊውን የማሻሻያ እርምጃ ይወስዳል፣
- የክልል መንግስት ሰራተኞች ሥነ-ምግባር መከታተያ ስርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፣ አፈጻፀሙን ይከታተላል፣
- የክልል መንግስት ሰራተኞች አስተዳደር ሕጎች በትክክል ስራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፣
- የመንግስት ዘርፍ አቅም ግንባታ ስራዎችን ያስተባብራል፣ የመንግስት ዘርፍ አገልግሎት በቀጣይነት የሚሻሻልበትና ውጤታማ የሚሆንበትን ስልት ይቀይሳል ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣
- የክልል መንግስት መስሪያ ቤቶችን አደረጃጀት አግባብነትን ይመረምራል፣ በአደረጃጀት ማሻሻያ ጥናቶች ላይ አስፈላጊውን ድጋፍ ይሰጣል፣
- በክልል መንግስት መስሪያ ቤቶች የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ፣ የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ሥርዓት መዘርጋቱንና ተግባራዊ መደረጉን ያረጋግጣል፣
- የፐብሊክ ሰርቪሱ የሰው ሃብት አመራርና የተቋማዊ መረጃዎች ሥርዓት በወጥነት እንዲዳብርና እንዲተገብር ያደርጋል ማዕከላዊ የመረጃ ምንጭ ሆኖ ያገለግላል፣
- የክልሉን የመንግስት መስሪያ ቤቶችን የሰው ሀብት አስተዳደር በበላይነት ይመራል፣ የስራ አመራር መመሪያዎችና የአፈፃፀም መስፈርቶችን ያዘጋጃል ያስፈፅማል፣
- የመንግስት ሰራተኞችን የደመወዝ፣ የልዩ ልዩ አበሎችና ጥቅማ ጥቅሞች ማሻሻያ ያጠናል ሲፈቀድም ስራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣
- በሕግ መሰረት የክልል መንግስት ሰራተኞችን ከጡረታ ዕድሜ ክልል በላይ በአገልግሎት ላይ ስለማቆየት በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፣
- በየደረጀው የሚታዩ የመልካም አስተዳደርና የኪራይ ሰብሳብነት ችግሮችን በጥናት መለየት፣ ለተለዩ ችግሮች ስልቶች መንደፍ፣ የአፈታት ሂደት መከታተልና መደገፍ፣ የፋይዳ ጥናት በማድረግ የህዝብ እርካታን ማረጋገጥ
- የመንግስት ሠራተኞችን አስተዳደር ፍርድ ቤት ያቋቁማል፣ ያደራጃል፣ አግባብ ባለው ሕግ መሠረት እንዲመራ ያደርጋል
- ዓላማውን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡