Skip to main content
zena2

የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሃብት ልማት ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት አፈፃፀሙን ገመገመ። በቀን 20/10/2016 የቢሮዉ ማናጅመንት ባደረገዉ ዉይይት የሴክተሩ የ2016 በጀት ዓመት አፈፃፀምና የ2017 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ ከሴክተሩ የዞንና የልዩ ወረዳ ሃላፊዎችና የዕቅድና በጀት ቡድን መሪዎች ጋር በጋራ እንዲገመገም ባስቀመጠዉ አቅጣጫ መሠረት ዛሬ ቅዳሜ 22/10/2016 በሆሳዕና ከተማ በመገምገም የበጀት ዓመቱ አፈፃፀም ላይ ተጨማሪ ግብዓቶችን በመስጠት አፀደቀ ፡፡ ለበጀት ዓመቱ ከተያዘዉ እቅድ በተጨማሪ በየደረጃዉ የሚገኝ የሁሉንም አመራርና ባለሙያ የትምህርት ማስረጃዎችን ህጋዊነት ለፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አደራጅቶ በመላክ ለማጣራት በተሰራዉ መረጃዎች የማሰባሰብ ስራ እንዲሁም የክልሉን የ2016 በጀት ዓመት የሰዉ ሃብት ስታስቲካል መረጃ ባጠረ ግዜ በማሰባሰብ መረጃዉን ለዉሳኔ ሰጪ አካላት ለማድረስ በየደረጃዉ በሚገኝ የሁሉም ተቋም አመራር፣ የሴክተሩ አመራርና ባለሙያዎች፣ የየመዋቅሩ የፊት አመራር ያበረከተዉ አስተዋፅኦ የላቀ እንደነበረ ተገምግሟል፡፡ በእለቱ የቢሮዉ ሃላፊ አቶ ገብሬ ጋጌ በሰጡት የስራ አቅጣጫ በበጀት ዓመቱ የሽግግር ወቅት ስራዎችን ከመደበኛ ስራ ጋር በማጣጣም 2 ዙር የ100 ቀናት ዕቅድ በማቀድ ሴክቶራሊ የተፈፀመበት መንገድ እንዲሁም በየሩብ አመቱ ዕቅድና ሪፖርቶችን በጋራ በመገምገም የተፈጠረዉ መግባባት በበጀት ዓመቱ ለተመዘገቡ አበረታች አፈፃፀሞች ጥሩ መደላድል የፈጠሩ በመሆኑ በ2017 በጀት አመትም ይህንን ጥሩ ልምድ አጠናክሮ በመደበኛ እቅድ አፈፃፀማችን እንደ ተሞክሮ በመዉሰድ የተፈጠረዉ መነሳሳት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ በመጨረሻም የሴክተሩ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ከየመዋቅሩ ለቢሮዉ ተከልሶ ሲላክ በዛሬዉ መድረክ የተሰጡ ግብዓቶችንና ቢሮዉ የላከዉን የመነሻ ዕቅድ እንደ ግብዓት በመጠቀም ከክልሉ ዕቅድ ጋር የግብና የዋና ዋና ተግባራት መናበብ ያለዉ እና የ2016 በጀት ዓመት አፈፃፀምን እንደቤዝ ላየን/መነሻ/ ይዞ ተከልሶ መዘጋጀት እንዳለበት የስራ መመሪያ ተሰጥቶ የእለቱ መድረክ ተጠናቋል፡፡