Skip to main content
zena3

ሐምሌ 6/2016 ቋሚ ኮሚቴው የክልሉን ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የ2016 በጀት አመት እቅድ ክንውን ገመገመ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የ2016 በጀት አመት እቅድ ክንውን ገምግሟል። የክልሉ ብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ አስቴር ይርዳው የ2016 በጀት አመት አፈጻጸም ሪፖርት ለቋሚ ኮሚቴው አቅርበዋል። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ መሰረት ወ/ሰንበት እና ሌሎች የቋሚ ኮሚቴው አባላት በቀረበው ዝርዝር ሪፖርት ላይ ተወያይተዋል።