የቢሮዉ ማናጅመንት የክልሉ ምክር ቤት በሰጠዉ ግብረ መልስ ላይ ዉይይት አደረገ (11/11/2016 ዓ/ም)። ሐምሌ 06/2016 ዓ/ም የክልሉ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቢሮዉን የ2016 በጀት ዓመት አፈፃፀም በዝርዝር መገምገሙ ይታወሳል፡፡ በግምገማዉ መድረክ የቋሚ ኮሚቴዉ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ መሰረት ወ/ሰንበት እና ሌሎች የቋሚ ኮሚቴው አባላት ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጥባቸዉ በለዪቸዉ ጉዳዮች ለቢሮዉ ማናጅመንት የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተዉ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ ከዚህም በመነሳት ቋሚ ኮሚቴዉ በቢሮዉ የ2016 በጀት ዓመት አፈፃፀም የነበሩ ጥንካሬዎችን፣ቀጣይ መሻሻል የሚገባቸዉን ጉዳዮችና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን የለየ የጽሁፍ ግብረ-መልስ ልከዋል፡፡ የቢሮዉ ማናጅመንት በተሰጠዉ ግብረ-መልስ ላይ ሰፊ ዉይይት ካደረገ በኋላ የቢሮዉ ሃላፊ ተወካይ ወ/ሮ አስቴር ይርዳ (ም/ቢሮ ሃላፊና የተቋማዊ ለዉጥና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ ) ባስቀመጡት አቅጣጫ የክልሉ ህዝብ የስልጣን ባለቤትነት መገለጫ የሆነዉ የተከበረዉ የክልሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጥንካሬ የለያቸዉን አፈፃፀሞች በቀጣዩ 2017 በጀት ዓመት ይበልጥ በማላቅ፣ማጽናትና ማዝለቅ እንዲሁም ቀጣይ መሻሻል እንደሚገባቸዉ የተለዩ አፈፃፀሞችንና ትኩረት እንደሚያሻቸዉ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አካል በማድረግ ማሻሻል እና በትኩረት መፈፀም እንደሚገባ የስራ መመሪያ የሰጡ ሲሆን የቢሮዉ ማናጅመንትም ግብረ-መልሱ በፍጥነት መላኩ እንዲሁም በቢሮ ደረጃ አጀንዳ ተደርጎ ዉይይት መደረጉ ለ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በበለጠ በትኩረት እንድንሰራ የሚያነሳሳ መሆኑን በማጠናከር ዉይይቱ ተጠናቋል፡፡