Fetehihawek
Tue, 06/16/2026 - 13:37
(ሆሳዕና፣ሰኔ 9/2018) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)በሆሳዕና ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መርቀው ስራ አስጀመሩ
በማዕከሉ በመጀመሪያ ዙር በ6 ተቋማት 20 አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑም ተመላክቷል።
በምረቃ መርሐ ግብሩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣፣የክልሉ ብሔረሰቦች ም/ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ፣የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ፣ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፈቃዱ፣በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክላስተር አስተባባሪዎች፣የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቲዎስ አኒዮ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።