Fetehihawek
Fri, 06/26/2026 - 13:08
(ዱራሜ ፣ሰኔ 19/2018)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በዱራሜ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መርቀው ስራ አስጀምረዋል፡፡ በማዕከሉ በመጀመሪያ ዙር በ6 ተቋማት 20 አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑም ተመላክቷል። በርዕሰ መስተዳድሩ የተመራው ልኡክ በማዕከሉ እየተሰጠ ያለውን አገልግሎት ተመልክተዋል። ይህ የዱራሜ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የክልሉን ፣ የወራቤን ፣ የወልቂጤን፣ የሆሳዕና እና የሃላባ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ተቋማት ጨምሮ በክልሉ 6ኛዉ ወደስራ የገባ ማዕከል ነዉ፡፡ በቀጣይ የሚመረቁ ማዕካለትን ጨምሮ በክልሉ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ተደራሽነት ለማስፋትና ይበልጥ ለማዘመን የክልሉ መንግስት በትኩረት እየሰራ የሚገኝ ሲሆን የማዕከላቱ መስፋፋት ቀድሞ በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ተገልጋዮች የሚነሷቸዉን ቅሬታዎችን በማስወገድ መልካም አስተዳደርን ለማስፈንና ብልሹ አሰራርን ከመሰረቱ ለመናድ ትልቅ አስተዋጽኦ ከማበርከታቸዉም በላይ ለሃገር በቀል ኢኮኖሚክ ሪፎርም /Home Grown Economic Reforem 2.0 / እና ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስኬት መደላድል ምቹ የሚፈጥሩ ይሆናል፡፡