Skip to main content
zena1

የቢሮዉ ማናጅመንት ዉይይት አደረገ ፡፡በቀን 20/10/2016 የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሃብት ልማት ቢሮ ማናጅመንት የሴክተሩን የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምንና የ2017 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ ገመገመ፡፡ በዉይይቱ የቢሮዉ የሰዉ ሃብት ልማትና ስራ አመራር ዘርፍ፣የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ድጋፍና ክትትል ዘርፍ፣የተቋማዊ ለዉጥና አቅም ግንባታ ዘርፍ እንዲሁም የአስተዳደር ፍርድ ቤቱ የ2016 በጀት ዓመት የተጠቃለለ ሪፖርት ቀርቦ ዉይይት የተደረገ ሲሆን በተጨማሪም የቢሮዉ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ዉይይት ተደርጓል፡፡ የተከበሩ አቶ ገብሬ ጋጌ (የቢሮዉ ሃላፊ) በሰጡት የስራ መመሪያ የ2016 በጀት ዓመት ሪፖርት ዘርፎች ሲያቀርቡ ሪፖርቱ ከዞኖችና ልዩ ወረዳዎች የመጡ የአፈፃፀም ሪፖርቶችንም ባካተተ መልኩ በተገቢዉ የተዘጋጀ መሆኑን ለማረጋገጥ የፊታችን ቅዳሜ ዕለት 22/10/2016 ከዞንና ልዩ ወረዳ የሴክተሩ ሃላፊዎችና የዕቅድና በጀት ቡድን መሪዎች ጋር የጋራ መድረክ ተፈጥሮ የቢሮዉ ማጠቃለያ ሪፖርትና የዞንና የልዩ ወረዳዎች ሪፖርት ቀርቦ ዉይይት ተደርጎ የሚሻሻሉ አፈፃፀሞችን በማካተት ሪፖርቱ ተጠቃሎ ለሚመለከታቸዉ አካላት በወቅቱ ተደራሽ እንዲደረግ አሳስበዋል፡፡ በተያያዘም የቢሮዉ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ የክልሉን የመልማት አቅም ባገናዘበ፣የ2016 በጀት ዓመትን ማጠቃለያ አፈፃፀምን እንደመነሻ የያዘ፣ዕቅዱን ለመፈፀም ያሉ አስቻይ ሁኔታዎችን በተገቢዉ የገመገመ እንዲሁም ከ7 ዓመቱ የሴክተሩ ዕቅድ ጋር በሚናበብ መልኩ የተዘጋጀ መሆኑን ማረጋገጥና ሴክቶራሊ ከዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ዕቅድ ጋር የግብ ማናበብና የግብ ስምምነት መፈራረረም ስለሚያስፈልግ እያንዳንዱ ዘርፍ ከታችኛዉ መዋቅር ጋር ግብና ዋና ዋና ተግባራትን የማናበብና ዕቅዱን ማዉረድ እንዳለበት አቅጣጫ የተሰጠ ሲሆን የተጠቃለለዉ የቢሮዉ ዕቅድም ወርዶ መድረክ በመፍጠር ከዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ጋር ሴክቶራሊ የግብ ስምምነት ማድረግ እንደሚገባ የስራ መመሪያ ተሰጥቶ የእለቱ መድረክ ተጠናቋል፡፡