የክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተቋማት አገልግሎት አሰጣጥና እየተከናወኑ ባሉ የልማት ስራዎች እያደረገ ያለውን የመስክ ምልከታ በሶስተኛ ቀን ውሎ በወልቂጤ ከተማ ተመልክቷል። (ሆሳዕና፦ ጥቅምት 30/2017) በመስክ ክትትልና ቁጥጥርም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ መነቴ ሙኒዲኖን ጨምሮ ከተለያዩ ዘርፎች የተወጣጡ የምክር ቤት አባላት ተገኝተዋል። የተደረገው ድንገተኛ የመስክ ክትትልና ቁጥጥር አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ተቋማት ለህብረተሰቡ ምን አይነት አገልግሎት እየሰጡ እንዳሉ ለማወቅ ያስችላል ሲሉ ወይዘሮ መነቴ ሙኒዲኖ ተናግረዋል። በመስክ ምልከታውም በግንባታ ህደት ያለው የወልቂጤ አጠቃላይ ሆስፒታል ተጠናቆ ለማህበረሰቡ አገልግሎት መስጠት ሲችል ሆስፒታሉ በበጀት እጥረት ምክንያት እየተጓተተ መሆኑን በምልከታ ለማውቅ ተችሏል። የወልቂጤ ከተማ ጤና ጣቢያ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ህብረተሰቡ ተረድተው መከላከል እንዲችሉ በቴለቪዥን ግንዛቤ እየተሰጠ መሆኑን ተመላክቷል። የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን ተጠቃሚዎች በተገቢ መልኩ አገልግሎት እያገኙ መሆናቸውን ከቀረበው መረጃ ማውቅ ተችሏል። የከተማው የኮርደር ልማት ተግባርን ለመጀመር የዲዛይን ስራ ተጠናቀው ወደ ተግባር ለመግባት ዝግጅት ላይ መሆኑ ተጠቁመዋል። መዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትን በማዘመንና የቴክኖሎጂ ስርዓትን በመዘርጋት ከወረቀት ንክክ ውጪ የሆነ አገልግሎት በመጀመሩ ተገልጋዮች ሳይጉላሉ በአንድ ጊዜ የሚፈለጉትን መረጃ እንዲያገኙ ማስቻሉን በምልከታው ከታዩ ጉዳዮች አንዱ ነው። የወልቂጤ መናኸሪያ አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ በተደረገው ሪፎርም ስራ በተቋሙ ጥሩ ለውጥ ማሳያቱንና በኢ_ትኬትንግ ለተሳፋሪዎች አገልግሎት እየተሰጠ እንደሚገኝ ተገልፀዋ። ተሳፋሪዎች ከታሪፍ በላይ እንዳይከፍሉ በመናኸሪያ ባለው ሚኒ ሚዲያ አማካኝነት ግንዛቤ እየተፈጠረ ሲሆን ህብረተሰቡ በትኬት ከተተመነ ታሪፍ ውጪ እንዳይከፍሉ እና ጥቆመ በመስጠት ሊተባበሩ ይገባል ተብሏል። ጽዱ አካባቢን ለመፍጠር በሀገር ደረጃ የተጀመረውን መነቃቃት ከዳር ለማድረስ የማህበረሰብ ጎዳና ዳር መጸዳጃ ቤት እየተሰራ ሲሆን የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓትም እየተከናወነ ቢሆንም የበለጠ መስራት እንደሚጠበቅም አስተያየት ተሰጥቷል ።