ለመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ባለሙያዎች በሥራ ሥነ-ምግባር ምንነት ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ
የካቲት 13/2018 (ሆሳዕና)
--------------------------------------------
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በርካታ የተለያዩ ተቋማት ተመጋጋቢ መንግስታዊ አገልግሎቶች በአንድ ማዕከል ተሰባስበዉ በቴክኖሎጂ በማቀላጠፍ እየተሰጡ ነው፡፡ የማዕከሉ አገልግሎት አሰጣጥ ተገልጋዮች ይገጥማቸዉ የነበረን በርካታ ውጣ ውረድ እና እንግልትን የሚያስቀር፤ ወጪ እና ጊዜን የሚቆጥብ እንዲሁም ብልሹ አሰራር እና ሌብነትን የሚያስቀር ነው፡፡
በክልሉ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት(ሆሳዕና)
1. ከንግድና ገበያ ልማት ቢሮ፡-አዲስ የንግድ ፈቃድ፣አዲስ የንግድ ምዝገባ፣ንግድ ፈቃድ እድሳት፣ንግድ ምዝገባ ማሻሻያ፣ንግድ ፈቃድ ማሻሻያ፣ንግድ ምዝገባ ምትክ፣ንግድ ፈቃድ ምትክ፣ተመለሽ ፍቃድ በድምሩ 8 አገልግሎቶች፤
2. ገቢዎች ቢሮ፡- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር
3. ፍትህ ቢሮ ፡-የውክልና ሰነድ ማረጋገጥ፣ ውክልና የመሻር/የመተው ሰነድ ማረጋገጥ፣ የሰነድን ኮፒ ከዋናው ጋር ማመሳከር፣የትርጉም ሰነድ ማረጋገጥ፣የፈቃደኝነት ማረጋገጫ ሰነድ ማረጋገጥ፣የቃለ-መሀላ ሰነድ ማረጋገጥ፣ የውጭ ሀገር ሰነድ መመዝገብ በድምሩ 7 አገልግሎቶች፤
4. ቴሌ፡- ቴሌ ብር አገልግሎት
5. ንግድ ባንክ፡- አካውንት ማውጣት ፣ ሲቢኢ ብር በድምሩ 2 አገልግሎቶች
6. ብሄራዊ መታወቂያ፡- ብሄራዊ መታወቂያ አገልግሎት
7. ኢትየጵያ ፖስታ፡- ፖስታ አገልግሎት፣ ብሄራዊ መታወቂያ አገልግሎት በድምሩ 2 አገልግሎቶች
8. የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፡- በ5 ቀናት አስቸኳይ ፓስፖርት እድሳት አገልግሎት፣ ጉዳት የደረሰባቸዉ እና ስህተት ያለባቸዉ ፓስፖርቶች አስቸኳይ ምትክ ፓስፖርት መስጠት አገልግሎት፣ ለጠፉና ለተሰረቁ ፓስፖርቶች አስቸኳይ ምትክ ፓስፖርት የመስጠት አገልግሎት ፣ ገፁ ያለቀ ፓስፖርት ዕድሳት አገልግሎት በድምሩ 4 አገልግሎቶች
በአጠቃላይ በማዕከሉ የ8 ተቋማት 27 አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ ታግዘዉ እየተሰጡ ሲሆን በተጨማሪም ከሌሎች ተቋማትም ተገልጋይ የሚበዛባቸዉ፣የተገልጋይ ቅሬታ ያለባቸዉን፣በክልል ማዕከል የሚሰጡ፣በቴክኖሎጂ ተሳስረዉ መሰጠት የሚችሉ አገልግሎቶችን በመለየት ወደ ማእከሉ ለማስገባት ስራዎች በመሰራት ላይ ናቸዉ፡፡
ማዕከሉ የተቋቋመለትን ቀልጣፋ አገልግሎቶችን ለተገልጋዮቹ የማቅረብ ዓላማ ለማሳካት የማዕከሉ ሰራተኞች የሥራ ሥነ-ምግባር ግንባታ መሰረታዊ ነዉ ፡፡ በመሆኑም የስራ ሥነምግባር ምንነትና የመልካም ሥራ ሥነ-ምግባር መገለጫዎች፣ የሥራ ሥነምግባር ማትሪክስ (matrix of work ethics)፣ መልካም የስራ ሥነ-ምግባር ባለቤት የሆኑ ሠራተኞች መለያ ባህሪያት፣ ከመሶብ የአንድ ማዕከል ሰራተኞች የሚጠበቁ የስራ ሥነ -ምግባራት ላይ ከክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሃብት ልማት ቢሮ በተጋበዙ ዳይሬክተር (በአቶ ፍትህአወቅ ፋንታሁን) የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
በስልጠናዉ ማጠቃለያ የማዕከሉ ሥራ-አስኪያጅ አቶ ከበደ ሻሜቦ ባስተላለፉት የስራ መመሪያ ሠራተኞች ከስልጠናዉ ያገኙትን ግንዛቤ በመጠቀም እርስ በእርስ ተደጋግፈዉ ዉጤታማ መሆን እንደሚገባቸዉና የተቋሙን የሥነ-ምግባር መመሪያ አክብረዉ በመስራት ከዚህም በበለጠ ተገልጋዮቻቸዉን በማርካት የተቋሙን መልካም ገጽታ መገንባት እንዳሚገባ አሳስበዋል ፡፡