Skip to main content
005

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (/ ) በተገኙበት  በሰባቱ የክልልክላስተር ማዕከል ከተሞች  'መሶብ'_ የአንድማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ግንባታን ማፋጠን በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ምከክር ተካሄደ 

ሆሳዕና የካቲት 23 2018 የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (/ ) በተገኙበት በሰባቱ የክልል ክላስተር ማዕከላት ከተሞች 'መሶብ'_ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ግንባታን ማፋጠን በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ውይይት ዛሬ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል።

ርዐሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው  (/) በመድረኩ ማጠቀሚያ እንደገለፁት በክልሉ በአሥራ ሰባት ከተሞች 'መሶብ '_የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ተደራሽ የማድረግ ዕቅድ ተይዞ እየተሠራ ነዉ።

'መሶብ'_የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ግንባታዉን በቅድሚያ በሰባቱ የክልል ክላስተር ማዕከል ከተሞች የመጀመር እንቅስቃሴ መጀመሩን ያመለከቱት ርዕሰ መስተዳድሩ ሥራውን በማፋጠንየአንድ ማዕከል አገልግሎቱን በአጭር ጊዜ ተደራሽ ለማድረግ ልዩ ክተትልና ድጋፍ እየተደረገ ነዉ ብለዋል።

የዲዛይን፣ የግንባታና መልሶ ግንባታ ሥራዎችን በማፋጠን የቴክኖሎጂ ዝርጋታና የፈርኒቸር አቅርቦት ሥራዎችን በማሳለጥ የአንድ ማዕከል አገልግሎቱን በአጠረ ጊዜ ለማስጀመር በቅንጅትና በፍጥነት ርብርብ እንዲደረግ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (/ ) አቅጣጫአስቀምጠዋል

ቀደም ሲል በክልል ደረጃ በሆሳዕና ከተማ  በተገነባው መሶብየአንድ ማዕከል አገልግሎት  ማዕከል  ዝግጅት  ወቅት በተግባርሂደት የተገኙ ልምዶችን በግብዓትነት መጠቀም እንደሚገባም ጠቁመዋል

በመድረኩ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተደድር የማህበራዊ ክላስተርአስተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ እና ሌሎች የክልል እና የዞን አመራሮች ተገኝተዋል።