Skip to main content
000010

(ቡታጅራ 10/10/2018 ዓ/ም) በማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል መንግስት የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ 6/2016 እና በዲሲፕሊንና ቅሬታ አቀራረብና አፈታት መመሪያ 17/2017 ለይ ሴክቶራሊ ለዞኖችና ልዩ ወረዳዎች የሰው ሃብት ልማትና ስራ አመራር በድን መሪዎች እንዲሁም የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ስብሳቢዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል ።

ስልጠናው በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት ተቋማት የሰው ሃይልን ለማስተዳደር የወጡ የህግ ማዕቀፎችን በተገቢው ተገንዝበው በመተግበርና በመተርጎም ወደክልሉ የመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር ፍርድ ቤት በይግባኝ መጥተው የሚሻሩ ውሳኔዎችን በመቀነስ በሚሻሩ ውሳኔዎች በውዝፍ የደመወዝ ክፍያ  የሚባክን ሃብትን እንዲሁም ይግባኝ በመጠየቅ የሚጉላሉ የመንግስት ሰራተኞችን እንግልት ማስቀረት ዓላማው ያደረገ ነው ።

በመድረኩ በየተቋሙ በሚገኙ የዲሲፕሊን ኮሚቴዎች  በአብዛኛው የትርጓሜ ስህተት በሚፈጠርባቸው የአዋጁ አንቀፃች ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና በቢሮው የሰው ሃብት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ይርጋለም ቲመርጋ እንዲሁም የዲስፕሊንና ቅሬታ አቀራረብና አፈታት መመሪያ 17/2017 በቢሮው የሰው ሃብት ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዓለሙ እንሲሶ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል ።