(ቡታጅራ፦ ሰኔ /21/2018) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በዌቭ 1 ወደ መንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የገቡ ቢሮዎች በዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ የሚመክር መድረክ በቡታጅራ ከተማ ተካሂዷል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ልዩ አማካሪ ንጉሴ አስረስ (ዶ/ር) እንደገለፁት ለህብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሪፎርም ስራዎችን ማጠናከር ይገባል። በሪፎርሙ የተነበቡ አደረጃጃቶችንና አሰራሮችን በመፍጠር ወደ ዋናው ትግበራ ለመግባት እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ የበለጠ በማጠናከር ወጥ ተግባራትን ለማከናወን መትጋት ያስፈልጋል ብለዋል።
የሪፎርሙን የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎችን በማጠናቀቅ ወደ ትግበራ ለመግባት እያንዳንዱ ተቋማት ተግባሩን በሚገባ በመምራት ለስኬታማነቱ በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል።ለህብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሪፎርም ስራዎችን ማጠናከር ለነገ የሚባል ተግባር እንዳልሆነ አስገንዝበዋል።
ሪፎርም የሚያደርጉ ተቋማት ምን ሪፎርም እንደሚደረግ በሚገባ በመረዳት እና በማወቅ ወጥ የሆነ አሰራሮችን በመዘርጋት ዕቅዶችንና ግቦችን መከለስ ያስፈልጋል ብለው ለተግባራቸው ግብረ መልስ ሊሰጣቸው ይገባል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ገብሬ ጋጌ በበኩላቸው የፐብሊክ ሰርቪስ አሰራሮችን በማዘመን ተቋማት ለዜጎች የሚሰጧቸውን የመንግስት አገልግሎቶችን ቀልጣፋና የተገልጋዩን እርካታ የሚያሳድጉ ሊሆን ይገባል ብለዋል።
ብዝኃነትና አካታችነትን የሚያረጋግጥ የፐብሊክ ሰርቪስ አሰራሮችን በመዘርጋት ቀልጣፋና ተደራሽ የመንግስት አገልግሎት ስርዓትን በማጠናከር የህዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ መረባረብ እንደሚገባ ገልፀዋል።
ዲጂታል የፐብሊክቨ ሰርቪስ አሰራሮችን በመዘርጋት አስፈጻሚውንና ፈጻሚ አካላት በቅንጅት በመስራት ለውጤታማነቱ መረባረብ ያስፈልጋል ብለዋል።በቀረቡ ዕቅዶች የወጥነት ክፍተት የሚታይ በመሆኑ ሁሉም ተቋማት ወጥ እና ሁሉንም ተግባራት ያካተተ ዕቅድ መዘጋጀት እንደሚገባ አሳስበዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች እንደገለፁት የሪፎርም ስራዎችን ተግባራዊ ለማድረግ በዝግጅት ምዕራፍ በርካታ ስራዎችን ማከናወናቸውን ነው የገለፁት።በቀጣይ በዝግጅት ምዕራፍ የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠልና ክፍተቶችን በማረም ወደ ትግበራ በመግባት የፐብሊክ ሰርቪስ ተግባራትን በማዘመን የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
በእለቱም በዌቭ 1 ወደ መንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የገቡ ቢሮዎች ጤና፣ ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ፣ፋይናንስ፣ቴክኒክና ሙያ ትምህርት እና ስልጠና፣ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እና ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የዝግጅት ምዕራፍ ዕቅድ ቀርበው በጠንካራና ደካማ አፈጻጸሞች ላይ ሀሳብና አስተያየት ተሰጥቶባቸዋል።