አቶ ገብሬ ጋጌ ግዴቦ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሃብት ልማት ቢሮ አገልጋይነትን የተላበሰና የመልካም አስተዳደር መርሆዎችን መሰረት አድርጎ በመስራት የተገልጋዩን እርካታ የሚያረጋግጥ ነፃ፣ገለልተኛና ብቃት ያለዉ ሲቪል ሰርቪስ በመገንባት በአጠቃላይ የክልሉን ሲቪል ሰርቪስ ስርዓት ለመቀየር እየሰራ ይገኛል፡፡
ቢሮዉ ቀጣይነት ባለው መልኩ የሲቪል ሰርቪስ ስርዓቱን ከአዲሱ ትዉልድ የሲቪል ሰርቪስ ፖሊሲ እና ከሃገራዊ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ጋር በተጣጣመ መልኩ በማላመድና በክልሉ በመተግበር የሲቪል ሰርቪስ ስርዓቱን ለዘመናት አንቀዉ ከያዙ ችግሮች በማላቀቅ ዘርፉን ለመቀየር የሚያስችሉ ተግባራትን በማከናወን ውጤታማ መሆን ይጠበቅበታል፡፡
በመሆኑም ቢሮዉ ቀልጣፋ የተቋማት አደረጃጀት እና የስራ ምዘና ስርዓትን የመዘርጋት፣የመልካም አስተዳደር መርሆዎች ትግበራን የማጠናከር፣ ተዓማኒነት ያለዉ ወቅታዊ የሰዉ ሃይል ስታስቲካል መረጃ የማጠናቀርና ተደራሽ የማድረግ፣የሰዉ ሃብት ህጎች አተገባበር ዉጤታማነትን የማሳደግ፣ ፣በየደረጃው የሚገኙ ተቋማት የአፈፃፀም ውጤታማነትን ማሳደግ እንዲሁም የአፈፃፀም ስራ አመራር ስርዓትን መተግበር ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሰራቸው ተግባራት ይሆናሉ፡፡ከዚህ በተጨማሪም የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያን በመተግበር ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት እንዲኖር በማድረግ ዘመናዊ ስርዓት...ተጨማሪ ያንብቡ
ዋና ዋና ዘርፎች
ዜና
(ቡታጅራ፦ ሰኔ/20/2018) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፐብሊክ… ተጨማሪ
(ዱራሜ ፣ሰኔ 19/2018)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በዱራሜ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መርቀው ስራ አስጀምረዋል፡፡ በማዕከሉ በመጀመሪያ ዙር በ6 ተቋማት 20 አገልግሎት… ተጨማሪ
(ሃላባ፣ሰኔ 16/2018) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)በሀላባ ቁሊቶ… ተጨማሪ
(ቡታጅራ 10/10/2018 ዓ/ም) በማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል መንግስት… ተጨማሪ
(ሆሳዕና፣ሰኔ 9/2018) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው… ተጨማሪ



















